መጋቢት 22/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የ2025 የብሔራዊ አካውንት ስርዓት (SNA) እና የክፍያ ሚዛን (Balance of payment BMP7) ላይ ከአፍሪካ አባል ሀገራት ከተውጣጡ የስታቲስቲክስ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የልማት ባንክና ዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ጋር የውይይት መድረክ መካሄድ ጀመረ።


በወርክሾፑ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ በረከት ፍስሀጽዩን የዚህ ዓይነት ወርክሾፕ በስታቲስቲክስ ዘርፍ ቅድሚያ መስጠት ያሉብንና ክፍተቶችን ለመለየት፣ ዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመለካት፣ አሁን ላይ ያለውን የስታቲስቲክስ ስርዓት ለማዘመን፣ በአህጉሪቱ የዕውቀት ሽግግርና እርሰ በዕርስ ለመማማር ያግዛል ሲሉ ገልፀዋል።

የዓለም ኢኮኖሚ በከፍተኛ ለውጥ ውስጥ እያለፈ በመሆኑ ዲጂታላይዜሽን እሴት የሚፈጥርበትን፣ የሚለወጥበትና የሚከፋፈልበት መንገድ እየተቀየረ ነው ሲሉ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ኃላፊ ሚስተር አዶም ጋጉሉም ገልፀዋል። በተጨማሪም ኃላፊው የ2025 የብሔራዊ አካውንት ስርዓትና የክፍያ ሚዛን አተገባበር ማሻሻያዎች የመለኪያ ማዕቀፎቻችን ወቅታዊ፣ ሁሉን አቀፍና ለታለመላቸው ዓላማ የሚመጥኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የተዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።


የዚህ መድረክ ዓላማ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ለመማር፣ የመረጃ ክፍተትና የተቋማት ቅንጅትን ማነስ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታትና የአፍሪካን ተጨባጭ ሁኔታ የሚመጥን የአተገባበር ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጅት ነው ያሉት የስታቲስቲክስ ዲቪዝን ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሻንታኑ ሙከርጄ ናቸው።


ወርክሾፑ በ2025 የብሔራዊ አካውንት ስርዓት (SNA) እና የክፍያ ሚዛን (Balance of payment BMP7) ላይ አዳዲስ የማክሮ ኢኮኖሚ የስታቲስቲክስ መመሪያዎችና ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀት ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።
