ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
በተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት ለሶስተኛ ጊዜ የዕውቀት ሽግግር መድረክ ተዘጋጅቶ የግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሠርቷል።

የተቋሙ የስታቲስቲክስ መረጃ ስርጭት እና ተደራሽነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ትግስት በቀለ በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የሥራ ክፍሎች ማንኛውንም ዕውቀት በአግባቡ መሰነድ እንዳለባቸው አንስተው፣ የዕውቀት ሽግግር የተቋሙ ባህል በማድረግ፣ ዕውቀትን መለዋወጥ እና ለተተኪ ትውልድ በተደራጀ መልኩ ማስተላለፍ የመድረኩ ዋና ዓላማ መሆኑን ገልፀዋል።

በተዘጋጀው መድረክ ላይ በህግ መሰረታዊ ሀሳቦች፣ የዲጂታል ላይብረሪ አጠቃቀምና እና ሪፖዚተሪ ሲስተም ላይ ገለጻ ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።


