ለተቋሙ ሰራተኞች በሰው ኃይል መረጃ ማረጋገጥ ስራ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር ተካሄደ

a3a2822

ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሚያካሂደው የመንግስት ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጥ ስራ ላይ ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር ተካሄደ።

a3a2812


በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ አቶ አወል አባመጫ የመንግስት ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጥ ስራውን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ተግባር መጠናቀቁን እና ተቋማችንም አንዱ የዚሁ አካል በመሆኑ መረጃ የማረጋገጥ ስራው በቋሚ የስራ መደብ ላይ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞችን የሚመለከት መሆኑን ገልፀው፤ በተቋሙ ያሉ ሰራተኞችም ይህንን በመገንዘብ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን እንዲያሟሉና መረጃ ሰብሳቢዎች በሚመጡ ጊዜ በአካል ተገኝተው አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

a3a2793


በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የመንግስት ሰራተኞች መረጃ የማረጋገጥ ስራ ዓላማ፣ ምን ዓይነት መረጃዎችን ይረጋገጣሉ፣ ከሰራተኛው ምን ይጠበቃል የሚለው ላይ ሰፊ ገለፃ ቀርቦ ግ ንዛቤ የተፈጠረ ሲሆን በገለፃው ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

a3a2795
a3a2824