ግንቦት 27/2018 ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እየተገበራቸው በሚገኙ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ከ26ቱ የስታቲስታክስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለተውጣጡ የአይቲ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤቢሳ አሰፋ ተቋማችን ዲጂታል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቆጠራና ጥናቶችን ጥራትንና ወቅታዊነት ለማስጠበቅ በሰፊው እየሰራ የሚገኝ መሆኑን እና በድጋፍ ዘርፉም መንግስት ባለማቸው ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች በበጀት አስተዳደር፣ በፋይናንስ አስተዳደርና አጠቃቀም፣ በንብረት አስተዳደርና አገልግሎት፣ በተሽከርካሪ ስምሪት፣ ጥገና እና ክትትል፣ በግዥ አፈጻጸም፣ በሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ስራዎችን እንዲሁም የሀብት ምዝገባን በዲጅታል ቴክኖሎጅ በመጠቀም አመርቂ ውጤቶችን እያስመዘገበ የሚገኝ መሆኑን አንስተው፤ የዛሬው ስልጠናም ተቋሙ እየሰራባቸው የሚገኙትን የሲቪል ሰርቪስ የተቀናጀ መረጃ አያያዝ ሥርዓትን (ICSMIS)፣ የሀብት ምዝገባ ማሳወቂያ ሲስተም፣ የተቀናጀ የፋይናንስ ሥራ አመራር ሥርዓት (IFMIS)ና የፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም ከዋናው መስሪያ ቤት እና በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወጥነትና ባለው ሁኔታ ወደስራ ለማስገባት መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚው በዚህ ስልጠና የተሳተፋቸሁ ባለሙያዎች ስልጠናውን በጥብቅ ዲስፒሊን በመከታተል ወደስራ ገበታችሁ ስትመለሱ ሁሉንም ሲስተሞች ስራ ላይ እንድታውሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ስልጠናው በተጠቀሱት ርዕሶች ላይ ከ26ቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ለቀጣይ አራት ቀናት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀግብር ለመረዳት ተችሏል።


