የ2019 ዓ.ም ግብርና ናሙና ጥናት የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።

ሐምሌ 15/11/2018 ዓ.ም ባቱ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየዓመቱ የሚያካሄደው የግብርና ናሙና ጥናት የቅድመ ዝግጅት ተግባራት አካል የሆነው የመረጃ ሰብሳቢዎች አሰልጣኝ ስልጠና በባቱ ከተማ በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ም/ዋ/ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ የ2019 ዓ.ም የግብርና ናሙና ጥናት ለማካሄድ የሚደረጉት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በሀገራችን ሁለተኛ ዙር ግብርና ቆጠራ ስራ በተሳካ ሁኔታ ባጠናቀቅንበት ማግስት የሚደረግ በመሆኑ አሰልጣኞች በቆጠራው ስራ ወቅት የተገኙ ልምዶች፣ ክህሎቶችንና የአዳዲስ አስቻይ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ለሰልጣኞች በማስገንዘብ መረጃ ሰብሳቢዎችን በብቃት የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞችን ለማብቃት መስራት እንዳለባቸው፤ ሰልጣኞች ስልጠናውን በዲስፕሊንና በትኩረት በመከታተል በቀጣይ ለሚጠበቅባቸው ስልጠና በቂ ዕውቀትና ልምድ ማካበት እንደሚጠበቅባችው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ለዘንድሮ የ2019 ዓ.ም አመታዊ የግብርና ናሙና ጥናት የሚሰጡት ስልጠናዎች ከሌላ ጊዜ በተለየ ሁኔታ በአንድ ጊዜና ወጥ በሆነ መልኩ የሚሰጥ በመሆኑ ከጥናቱ የሚገኙትን የስታቲስቲክስ ሪፖርቶች በታቀደላቸው የጊዜ ገደብ ለመንግስትና ለተጠቃሚዎች ለማድረስ እንደሚያስችል የግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዱላዚዝ ሽፋ ገልጸዋል።

ስልጠናው ከሐምሌ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ 15 ቀናት በጥናቱ ንድፈ ሀሳብና ተግባር ላይ አተኩሮ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከ27 ቅ/ጽ/ቤቶች የተውጣጡ የዴክስ ኃላፊዎች፣ስታቲስቲሺያኖችና የአይቲ ባለሙያዎች በአጠቃላይ 408 ባለሙያዎች በስልጠናው ላይ ይሳተፋሉ፡፡

a3a9215
a3a9180
a3a9196