ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም ባቱ
ባለፉት15 ቀናት በባቱ ከተማ በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የ2019 ዓ.ም የግብርና ናሙና ጥናት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።
በስልጠናው መዝጊያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የተቋሙ ም/ዋ/ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ በስልጠናው ወቅት የተገኙትን ልምድና ዕውቀት በቀጣይ ለምታሰለጥኑት መረጃ ሰብሳቢዎች በተሟላ መልኩ በማካፈል ለመስክ ስራው ብቁ የሰው ሀይል ለማዘጋጀት በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ለሰልጣኞች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።



