በተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

ለኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያቤትና ለ26 ቅ/ጽ/ቤቶች ሰራተኞች ዕምርታ በስታቲስቲክስ ልማት በሚል ርዕስ በተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ላይ አተኩሮ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ የሚሰጠው ስልጠና ተጀመረ፡፡

በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በስልጠና ውይይቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት በመካካለኛ ዘመን የስታቲስቲክስ ልማት የተሰሩት ተግባራትና የተገኙት ውጤቶችን በመገምገም፤ ከ2019_ 2021 ዓ.ም ስለሚተገበረው የስታቲስቲክስ ልማት አቅጣጫ በውል በመገንዘብ በጋራ፣ በአንድነት ለመተግበር የተሟላ ግንዛቤና ዕውቀት እንዲኖረን የሚያስችለን ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩራትና በዲሲፕሊን በመከታተል ለቀጣይ ተልዕኮ ራሳቸውን ማዘጋጃት እንደሚጠበቅባችው የስራ መመሪያ በመስጠት ስልጠናውን አስጀምረዋል።

a3a0937
a3a0931
a3a0911
a3a0924
a3a0922
a3a0938