ነሐሴ 16/2018ዓ.ም፤ ጅማ ከተማ
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በጅማ ከተማ ጉዳታ ቡላ ቀበሌ በመገኘት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ስራ አስጀመሩ።
ቀበሌው ተገኝተው የክረምት በጎ አድራጎት ስራውን ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የዚህ ዓመት የበጎ አድራጎት ስራ ለማስጀማር ከአዲስ አበባ 150 የተቋሙ ሰራተኞች ይዘን ወደ ጅማ ከተማ ስንመጣ ፣ችግኝን በመትከል በህዝቦች ውስጥ የመልማት ተስፋን ለመትከል፣ቡኡራ ቦሩ ቅድማ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት በመገንባት የነጌውን ትውልድ በዕውቀት ለመገንባት ፣ህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለመጠናከርና ከለን ላይ ሰባአዊ ድጋፍ የመድረግ አራት ግቦች ለመሳከት ተሳቢ በመድረግ እንደሆና አስረድተው በከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመርና ጉዳታ ቡላ ቀበሌ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ ሁሉንም ግቦች መሳካት መቻሉ ገልጾው ተቋማቸው በጉዳታ ቡላ ቀበሌ የሚገነባውን ኡርጅ ጅማ ቡኡራ ቦሩ ቅድማ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት ግንባታ በአጠረ ጊዜ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ቃል ገብቷው ስራውን ለማስጀመር ወደ ከተማው ሲመጡና በነበራቸው ቆይታ በከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመር ፣ በከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት አመረሮችና ጉዳታ ቡላ ቀበሌ ነዋሪዎች ለተደረገላቸው ደማቅና ቤተሰባዊ አቀባበል በተቋማቸው ስም የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመር የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በከተማቸው ጉዳታ ቡላ ቀበሌ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ስራ ለማከናወን ወስኖ በመካከላቸው በመገኘታቸው ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና በማቅረብ የተጀመረው ኡርጅ ጅማ ቡኡራ ቦሩ ቅድማ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት ግንባታበአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለሚፈለገው አገለግሎት እንዲውል ክትትልና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
በ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ስራው በከተማው ጉዳታ ቡላ ቀበሌ አንድ ኡርጅ ጅማ ቡኡራ ቦሩ ቅድማ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት ግንባታ የማስጀመርና 200 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የመድረግ ተግባራት ተከናውኗል።
ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና ከጅማ ቅ/ጽ/ቤት የተውጣጡ 200 ሠራተኞች ሰራተኞች ተሳትፈዋል።




