በሲዳማ ክልል የመንግስት ሠራተኞች መረጃ የማረጋገጥ ጥናት ላይ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም ባቱ

ኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፌዴራል ሲቨል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል በሚያካሂደው የክልል የመንግስት ሠራተኞች ፕርሶኔል መረጃ የማረጋገጥ ጥናት ላይ ለሚሳተፉ መረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጠሪዎች በባቱ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተሻገር መንግስት ዘመናዊ ሲቨል ሰርቪስ ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት የሰው ሀይሉ የተሟላና ትክክለኛ መረጃ አስፈላጊ በመሆኑ በመላው ሀገራችን የመንግስት ሠራተኞችን ፕርሶኔል መረጃ የመረጋገጥ ጥናት እየተከናዋነ መሆኑ አስረድተው በሲዳማ ከልል የሚካሄደው የመንግስት ሠራተኛች ፕርሶኔል መረጃ የመረጋገጥ ጥናት በተሳካ መልኩ ለማጠናቀቅ ሰልጠኞች ለስልጠናው ተገቢ ትኩረት በመስጠት ለመስክ ስራው የሚያስፈልጋቸውን ግንዛቤና ዕውቀት መጨበጥ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሀገራችን ዲጂታል 2030 ራዕይ እውን ለማድረግ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የገለጹት የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግስቱ ማቲዮስ በክልላቸውም ዲጂታል ሲቨል ሰርቪስ ለመገንበት እየተሰሩ የሚገኙት ስራዎች ለማሳካት ጥራት ያለው የክልሉ የመንግስት ሠራተኞች መረጃ የሚጠይቅ በመሆኑ የስልጠናው ተሳታፊዎች ከስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀት በዲሲፕሊን ተግባራዊ በማድረግ ስራውን ለማሳካት በትጋት መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ስልጠናው ከሐምሌ22_ነሐሴ 2/2018 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች የተወጣጡ 700 ሰልጣኞች በስልጠናው ይሳተፋሉ።

a3a0177
a3a0071
a3a0083
a3a0134
a3a0165
a3a0155
a3a0075