ብሔራዊ የምርምር ልማት ወጪ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

ሰኔ 26/10/2018 አዳማ

የኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፌደራል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ በሚያካሄዱት ብሔራዊ የምርምር ልማት ወጪ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካት ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የምርምር ልማት ለአንድ ሀገር ዕድገት መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አስረድተው ቀጣይ ለሚሰሩ የምርምር ልማት ስራዎች የዘርፉ አሁናዊ መረጃ ማወቅ አስፈላጊ በመሆኑ ሁለቱ ተቋማት ብሄራዊ የምርምር ልማት ወጪ ጥናት በጋራ ለማካሄድ እየሰሩ መሆኑ ታውቆ ከጥናቱ የሚፈለገው መረጃ እንዲገኝ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ምክትል ዋ/ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ ከብሔራዊ የምርምር ልማት ወጪ ጥናት የሚገኙት መረጃዎች ለሀገር ያለቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው መድረኩ ለጥናቱ በተዘጋጁ ሜቶዶሎጂ፤መጠየቅና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ከመድረኩ የተገኙትን ግብዓቶች በማካተት ወደ ስራ ለመግባት የተዘጋጀ መድረክ በመሆኑ ተሳታፊዎች ለጥናቱ በተዘጋጁ ማኑዋሎች ላይ በቂ ሀሳብ በመስጠት እንዲያጠናክሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ከፌዴራል ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ከግል ቢዝነስ ተቋማት፤ከልማት አጋር ድርጅቶችና ከሙያ ማህበራት የተውጣጡ ከፍተኛ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ለጥናቱ በተዘጋጁት ማኑዋሎች ላይ ያተኮረ ውይይት ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ይካሄዳል፡፡

a3a7511
a3a7466
a3a7520
a3a7476